ስለ OCTFME በጥቂቱ (Amharic)

ስለ OCTFME በጥቂቱ
 
ስለ የኬብል ቴሌቪዥን፣ ፊልም፣ ሙዚቃ እና መዝናኛ ቢሮ (Office of Cable Television, Film, Music and Entertainment (OCTFME)) በጥቂቱ
ተልእኮ
የኬብል ቴሌቪዥን፣ ፊልም፣ ሙዚቃ እና መዝናኛ ቢሮ (Office of Cable Television, Film, Music and Entertainment (OCTFME)) ተልእኮ ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሕዝብ፣ የትምህርት፣ እና የመንግስት ተደራሽነት (ፒኢጂ፣ PEG) የኬብል ጣቢያዎች እና የዲጂታል ሬዲዮ ጣቢያ መርሃ-ግብር ማዘጋጀት እና ማሰራጨት፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የኬብል ቴሌቪዥን አገልግሎት አቅራቢዎችን መቆጣጠር፣ ለኬብል ተመዝጋቢዎች የደንበኞች አገልግሎት መስጠት፣ እና በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ስራ ፈጣሪ ኢኮኖሚ እና የስራ ኃይል ገበያ መደገፍ ነው።
 
የአገልግሎት ማጠቃለያ
OCTFME በዲስትሪክቱ ውስጥ ኬብል ቴሌቪዥንን የመቆጣጠር እና የዲስትሪክቱን የመንግስት ተደራሽነት ቻናሎችን የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት፥ የዲስትሪክት ካውንስል ቻናል (District Council Channel (DCC))፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ኔትወርክ (District of Columbia Network (DCN))፣ የዲስትሪክት የእውቀት ኔትወርክ (District Knowledge Network (DKN)) እና የዲሲ ሬዲዮ 96.3HD4። OCTFME በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሕዝብ፣ ትምህርታዊ፣ እና የመንግስት (ፒኢጂ፣ PEG) ቻናሎች እና ሌሎች የመረጃ ምንጮች በኩል ተመልካቾችን የሚያሳውቁ፣ የሚያስተምሩ እና የሚያዝናኑ ይዘቶችን ይፈጥራል። ሽልማት አሸናፊ የሆነው ይዘት ስለ መንግስት እንቅስቃሴ፣ ስለ ትምህርት፣ ወቅታዊ ክስተቶች፣ ታሪክ፣ እና ስነጥበብና መዝናኛ መረጃን ያቀርባል።

OCTFME በዲስትሪክት ካውንስል ቻናል (District Council Channel (DCC))፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ኔትወርክ (District of Columbia Network (DCN))፣ እና የዲስትሪክት የእውቀት ኔትወርክ (District Knowledge Network (DKN)) ላይ የ 24-ሰዓት መረጃ ሰጭ፣ ግልጽ የሆነ መንግስት፣ የህዝብ ፍላጎት ላይ የሚያተኩሩ ፕሮግራሞች ያቀርባል። ፕሮግራሙ የከተማው ከንቲባ ስራ አስፈጻሚ ቢሮዎች እና ስራ አስፈፃሚ ቅርንጫፎች ሽፋን፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ከተማ ምክር ቤት፣ የአቃቤ ህግ ጽ/ቤት፣ እና የስቴት የትምህርት ቦርድን ያጠቃልላል። OCTFME በዲስትሪክቱ ውስጥ ስለሚደረግ የመንግስት የስራ ሂደት እና በዲስትሪክቱ ውስጥ ህይወት ምን እንደሚመስል ግልጽ የሆነ ለሕዝብ ተደራሽነት ይሰጣል። OCTFME የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ነዋሪዎችን የሚያስተምሩ፣ የሚያሳውቁ፣ እና የሚያጠናክሩ የተለያዩ ጥራት ያላቸው ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ለመስጠት ቆርጦ ይሰራል።

OCTFME በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኘው WHUR ጋር በመተባበር የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የመጀመሪያ እና ይፋ የመንግስት የዲሲ ሬዲዮ 96.3 HD4 ን ያስተዳድራል። በጣቢያው የሚቀርቡት ፕሮግራሞች በጣም ወሳኝ የሆኑ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ የድንገተኛ ጊዜ እና ድንገተኛ ላልሆኑ አገልግሎቶች እና ማስጠንቀቂያ ላይ የሚሰሩ ፕሮግራሞች በማጋራት፣ በተጨማሪም የማህበረሰብ እና የመንግስት ጉዳዮች ፕሮግራሞችን በማቅረብ የዲስትሪክቱን ነዋሪዎች የኑሮ ጥራት ያሳድጋል። በተጨማሪም፣ የዲሲ ሬዲዮ 96.3 HD4 ለዲሲ ነዋሪዎች እና ተማሪዎች የሚዲያ ግንዛቤ ማሰልጠኛ መድረክ ይሰጣል።

OCTFME ለአካባቢያዊ እና ከስቴት ውጪ ላሉ የፊልም፣ ቴሌቪዥን፣ ቪዲዮ፣ መዝናኛ፣ አሳታፊ፣ መልቲሚዲያ፣ እና ዲጂታል ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የሚከተሉትን ጨምሮ በርካታ የድጋፎ አገልግሎቶችን ይሰጣል፥ የሚዲያ ዝግጅት ፍቃድ መስጠት፣ ተስማሚ ቦታ መፈለግ፣ የፕሮግራም ዝግጅት ድጋፍ፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና የመሰረተ ልማት ማበረታቻዎች፣ የስራ ምደባ ድጋፍ፣ እና የስራ ኃይል ልማት ፕሮግራሞች። OCTFME ከዚህ በተጨማሪም፣ የዲሲ የፊልም፣ የቴሌቪዥን እና የመዝናኛ ራባት ፈንድ የተሰኘውን የሚዲያ ዝግጅት ማበረታቻ ፕሮግራምን ያስተዳድራል።

OCTFME በጥቅሉ ስራ ፈጣሪ ስለሆነው ኢኮኖሚ ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ የሚዲያ ዝግጅቶች የመፍጠር ሂደት፣ እና በገበያ ተፈላጊ የስራ ፈጣሪ የኢኮኖሚ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸውን የስልጠና እድሎች ተደራሽነት እንዲኖር ለማድረግ ማህበረሰቡን ያሳትፋል።

View information about the Language Access Program